የታለች ያቺ ወፍ
ያኔ
ልጅ እያለሁ - ሰላም የምትለኝ
በሚያስደምም
ዜማ - ልቤን የምትቃኘኝ
ቀኑ
ደስ እንዲለኝ - ተስፋ የምትሰጠኝ
የታለች
ያቺ ወፍ? - ዛሬ ስትናፍቀኝ ::
ከእንቅልፌ
ስነቃ - ደስ በሚለው ዜማ
ኮለል
ብሎ መጥቶ - በጆሮዬ ሲሰማ
የቀኑን
ብሩህነት - ለነብሴ አብስራ
ታነቃቃኝ
ነበር - መንፋሴን አድሳ ::
የታለች
ያቺ ወፍ? - ዛሬ ስፋልጋት
ምነው
አልዘፈነች - ነብሴ ሲናፍቃት ::
ምናል
ብትመጣ - ልትሰጠኝ እርካታ
ዜማውን
አፍልቃ - ብትሆነኝ እርጋታ ::
ግና
ብትመጣስ - እንግባባ ይሆን
እንዲህ
ተለያይተን - ብዙ አመቶች ከርመን ::
አንድ
ያመሳሰለን - ጓደኞች ያረገን
የዋህነት
ነበር - በፍቅር ያቀረበን ::
አሁን
ታደገና - የዋህነት ቀርቷል
እንደ
እባብ በተንኮል - መተያየት በዝቷል
መተዛዘን
ቀርቶ - መጠቃቀም ሆኗል
ሀሳብ
ና ልብም
- ሲባክን ይውላል ::
አሁን
ወፏ መጥታ - ጓደኞቿን ጠርታ
ስትዘፍን
ብትወል - ኦርኬስትራ ሰርታ
ማን
ሊያዳምጣት ነው - በበዛ ጫጫታ
ማንስ
ይሰማታል - ታስረን በሁካታ ::
Wow, I love it... a lot. Ananya, I really enjoyed this one... you really inspire me...maybe I will paint something to go with your poem and with your permission of course... I will love to post it on my blog...let me know. May God bless you.. yeni geta
ReplyDelete