Wednesday, February 26, 2014

Gitme 2



የሰው ልጅ

                ከአንገቱ አቀርቅሮ - መሬቱን እያየ
ከልቡ እንደከፋው - በእንስሶቹ ታየ
                እንሶቹም ቀርበው - ጥያቄ  ጠየቁት
                ሊረዱት ፈልገው - ብዙ አፋጠጡት
እንሶቹ:    የሰው ልጅ ምነካህ -ለምን ተክዘሀል
                 በሞላ አለም ውስጥ - ምን ያስጨንቅሀል?”
ሰው:        እንዴት አላቀርቅር - እንዴትስ አይክፋኝ
                እኔ ምስኪኑ ሰው - ምንም ነገር የለኝ’
እናንተ ሁላችሁ - ስጦታ አላችሁ
በዚህም ምክንያት - ደስተኞች ሆናችሁ::”
ዝሆን:      አንተን ካስደሰተህ - ካረካው ልብህን
ያለንን ብንሰጠህ - ምንም አይገደንም::”
ሰው:        እኔ ደካማ ነኝ - ምንም ሀይል የለኝ
ከግርማ ሞገሱም - አንዳች አልተሰጠኝ::”
አንበሳ:     እኔ ጠንካራ ነኝ - የሁሉም ንጉስ ነኝ
ከሀይሌም ግማሹን - ብሰጥህ አይከብደኝም::”
ሰው:        ሀይልን በማግኘቴ - ደስተኛ ብሆንም
                አርቆ ማየቱን - አይኖቼ አይችሉም::”
አሞራ      ማነው እንደ አሞራ - ከሩቁ የሚያየው
                ሰማዩን አቋርጦ - መሬት የሚያስሰው
                ከሩቅ አሳ አይቶ - ጠልቆ የሚበላው
                እኔ ነኝ በአይን - ከሁሉ የምበልጠው
                እንደ እኔ እንድታይ - እንካ አይኔን ውሰደው::”
                ከእባብ እውቀቱን - ከጦጣም ብልሀትን
                ከዶሮ ጫጩትን - ከላምም ወተትን
                ከእንስሶቹ ሁሉ - ወስዶ ችሎታውን
                አመስግኖ ሄደ - ተሰናብቶ ሁሉን

ቆቅ:          አሁን ልቤ ፈራ - በጣሙን ታወቀኝ
                የሰው ልጅ ተንኮሉ - መንፈሶቹ ታየኝ::”
ሚዳቋ:    ኸረ ከቶ አትፍሪ - እሱ ደስተኛ ነው
                ሁሉን ስላገኘ - እንደ እኛ ሰላም ነው::”
ቆቅ:          አይኖቼ አትኩረው - የሰውን ልብ ሳየው
                ትልቅ ቀዳዳ ያለው - ባዶነት ህይወት ነው
ሁሉን ቢያከማቹም - ንብረት ቢጨምሩም
                ያን ቀዳዳ ሞልተው - አንዳችም አይረኩም::”

አናንያ

No comments:

Post a Comment