የሰው
ልጅ
ከአንገቱ አቀርቅሮ - መሬቱን እያየ
ከልቡ እንደከፋው - በእንስሶቹ ታየ
እንሶቹም ቀርበው - ጥያቄ ጠየቁት
ሊረዱት ፈልገው - ብዙ አፋጠጡት
እንሶቹ: “የሰው ልጅ
ምነካህ -ለምን ተክዘሀል
በሞላ አለም
ውስጥ - ምን ያስጨንቅሀል?”
ሰው: “እንዴት አላቀርቅር - እንዴትስ አይክፋኝ
እኔ ምስኪኑ ሰው - ምንም ነገር የለኝ’
እናንተ ሁላችሁ - ስጦታ አላችሁ
በዚህም ምክንያት - ደስተኞች ሆናችሁ::”
ዝሆን: “አንተን ካስደሰተህ - ካረካው ልብህን
ያለንን ብንሰጠህ - ምንም አይገደንም::”
ሰው: “እኔ ደካማ ነኝ - ምንም ሀይል የለኝ
ከግርማ ሞገሱም - አንዳች አልተሰጠኝ::”
አንበሳ: “እኔ ጠንካራ
ነኝ - የሁሉም ንጉስ ነኝ
ከሀይሌም ግማሹን - ብሰጥህ አይከብደኝም::”
ሰው: “ሀይልን በማግኘቴ - ደስተኛ ብሆንም
አርቆ ማየቱን - አይኖቼ አይችሉም::”
አሞራ “ማነው እንደ አሞራ - ከሩቁ የሚያየው
ሰማዩን አቋርጦ - መሬት የሚያስሰው
ከሩቅ አሳ አይቶ - ጠልቆ የሚበላው
እኔ ነኝ በአይን - ከሁሉ የምበልጠው
እንደ እኔ እንድታይ - እንካ አይኔን ውሰደው::”
ከእባብ እውቀቱን - ከጦጣም ብልሀትን
ከዶሮ ጫጩትን - ከላምም ወተትን
ከእንስሶቹ ሁሉ - ወስዶ ችሎታውን
አመስግኖ ሄደ - ተሰናብቶ ሁሉን
ቆቅ: “አሁን ልቤ ፈራ - በጣሙን ታወቀኝ
የሰው ልጅ ተንኮሉ - መንፈሶቹ ታየኝ::”
ሚዳቋ: “ኸረ ከቶ
አትፍሪ - እሱ ደስተኛ ነው
ሁሉን ስላገኘ - እንደ እኛ ሰላም ነው::”
ቆቅ: “አይኖቼ አትኩረው - የሰውን ልብ ሳየው
ትልቅ ቀዳዳ ያለው - ባዶነት ህይወት ነው
ሁሉን ቢያከማቹም - ንብረት ቢጨምሩም
ያን ቀዳዳ ሞልተው - አንዳችም አይረኩም::”
አናንያ