Wednesday, February 26, 2014

Gitme 2



የሰው ልጅ

                ከአንገቱ አቀርቅሮ - መሬቱን እያየ
ከልቡ እንደከፋው - በእንስሶቹ ታየ
                እንሶቹም ቀርበው - ጥያቄ  ጠየቁት
                ሊረዱት ፈልገው - ብዙ አፋጠጡት
እንሶቹ:    የሰው ልጅ ምነካህ -ለምን ተክዘሀል
                 በሞላ አለም ውስጥ - ምን ያስጨንቅሀል?”
ሰው:        እንዴት አላቀርቅር - እንዴትስ አይክፋኝ
                እኔ ምስኪኑ ሰው - ምንም ነገር የለኝ’
እናንተ ሁላችሁ - ስጦታ አላችሁ
በዚህም ምክንያት - ደስተኞች ሆናችሁ::”
ዝሆን:      አንተን ካስደሰተህ - ካረካው ልብህን
ያለንን ብንሰጠህ - ምንም አይገደንም::”
ሰው:        እኔ ደካማ ነኝ - ምንም ሀይል የለኝ
ከግርማ ሞገሱም - አንዳች አልተሰጠኝ::”
አንበሳ:     እኔ ጠንካራ ነኝ - የሁሉም ንጉስ ነኝ
ከሀይሌም ግማሹን - ብሰጥህ አይከብደኝም::”
ሰው:        ሀይልን በማግኘቴ - ደስተኛ ብሆንም
                አርቆ ማየቱን - አይኖቼ አይችሉም::”
አሞራ      ማነው እንደ አሞራ - ከሩቁ የሚያየው
                ሰማዩን አቋርጦ - መሬት የሚያስሰው
                ከሩቅ አሳ አይቶ - ጠልቆ የሚበላው
                እኔ ነኝ በአይን - ከሁሉ የምበልጠው
                እንደ እኔ እንድታይ - እንካ አይኔን ውሰደው::”
                ከእባብ እውቀቱን - ከጦጣም ብልሀትን
                ከዶሮ ጫጩትን - ከላምም ወተትን
                ከእንስሶቹ ሁሉ - ወስዶ ችሎታውን
                አመስግኖ ሄደ - ተሰናብቶ ሁሉን

ቆቅ:          አሁን ልቤ ፈራ - በጣሙን ታወቀኝ
                የሰው ልጅ ተንኮሉ - መንፈሶቹ ታየኝ::”
ሚዳቋ:    ኸረ ከቶ አትፍሪ - እሱ ደስተኛ ነው
                ሁሉን ስላገኘ - እንደ እኛ ሰላም ነው::”
ቆቅ:          አይኖቼ አትኩረው - የሰውን ልብ ሳየው
                ትልቅ ቀዳዳ ያለው - ባዶነት ህይወት ነው
ሁሉን ቢያከማቹም - ንብረት ቢጨምሩም
                ያን ቀዳዳ ሞልተው - አንዳችም አይረኩም::”

አናንያ

Tuesday, February 25, 2014

Gitme

                                                  

            የታለች ያቺ ወፍ
ያኔ ልጅ እያለሁ - ሰላም የምትለኝ
በሚያስደምም ዜማ - ልቤን የምትቃኘኝ
ቀኑ ደስ እንዲለኝ - ተስፋ የምትሰጠኝ
የታለች ያቺ ወፍ? - ዛሬ ስትናፍቀኝ ::
ከእንቅልፌ ስነቃ - ደስ በሚለው ዜማ
ኮለል ብሎ መጥቶ - በጆሮዬ ሲሰማ
የቀኑን ብሩህነት - ለነብሴ አብስራ
ታነቃቃኝ ነበር - መንፋሴን አድሳ ::
የታለች ያቺ ወፍ? - ዛሬ ስፋልጋት
ምነው አልዘፈነች - ነብሴ ሲናፍቃት ::
ምናል ብትመጣ - ልትሰጠኝ እርካታ
ዜማውን አፍልቃ - ብትሆነኝ እርጋታ ::
ግና ብትመጣስ - እንግባባ ይሆን
እንዲህ ተለያይተን - ብዙ አመቶች ከርመን ::
አንድ ያመሳሰለን - ጓደኞች ያረገን
የዋህነት ነበር - በፍቅር ያቀረበን ::
አሁን ታደገና - የዋህነት ቀርቷል
እንደ እባብ በተንኮል - መተያየት በዝቷል
መተዛዘን ቀርቶ - መጠቃቀም ሆኗል
ሀሳብ ና ልብም - ሲባክን ይውላል ::
አሁን ወፏ መጥታ - ጓደኞቿን ጠርታ
ስትዘፍን ብትወል - ኦርኬስትራ ሰርታ
ማን ሊያዳምጣት ነው - በበዛ ጫጫታ
ማንስ ይሰማታል - ታስረን በሁካታ ::